(Vie et mœurs d’oiseaux d’Ethiopie) (የኢትዮጵያ ወፎች ሕይወት እና ወግ) @ PEIRE FREDERIC ART-THERAPIE

Le premier contact avec les oiseaux d’Ethiopie fut durant la saison des pluies, où sous un vacarme de vieille guimbarde, le lourd envol d’un couple d’ibis me surpris. Profitant d’un séjour confiné lors de la Covid à l’ambassade de France d'Addis Abeba, je décidai d’en rapporter les anecdotes, en croquant à l’aquarelle leurs vies au fil des saisons.

ከወፎች ጋር ያለኝ ግንኙነት አዲስ አይደለም። እኔ እስከማስታውሰው ድረስ፣ በአጽናፈ ዓለማችን መካከል ምንም አይነት አለመግባባትን የሚፈጥር እንቅፋት እንደሌለ ሁልጊዜ ይሰማኝ ነበር። ስለዚህ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ፣ የወፎችን ቋንቋ መረዳት ለኔ ፍፁም ተፈጥሯዊ ነበር። ስለዚህ፣ በቅርቡ የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ በቤት ውስት ተዘግቶ መቀመጥ ግዴታ በነበረበት ወቅት በአዲስ አበባ በሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ ሰፊ የአትክልት ስፍራና ጫካ ውስጥ የነበረኝን ቆይታ ተጠቅሜ በስፍራው የሚኖሩትን ወፎች ህይወትና በተለያዩ ወቅቶች በክረምቱም በጸደይም ሆነ በበጋው የተፈጠሩትን ታሪኮች በውሃ ቀለም በመሳል ለማውጋት ወስኜ ስዬ አቅርብያለሁ።